am_tn/pro/07/04.md

1.4 KiB

ጥበብን አንቺ እኅቴ ነሽ በላት

እዚህ ላይ ጥበብ ሰው እንደሆነች ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እህትህን እንደምትወድ እንደዚሁ ለጥበብ ተገቢ ዋጋ ስጣት” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማስተማውልንም ወዳጄ ብለህ ጥራት

እዚህ ላይ የማስተዋልን ባሕርይ እንደ ወዳጅ ወይም ዘመድ ተገልጧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወዳጅህን እንደምትንከባከብ እንደዚሁ ማስተዋልን ተንከባከባት” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወዳጅ

“ዘመድ” ወይም “የቤተሰብ አባል”

ጋለሞታ ሴት

ይህ አንድ ወንድ ጋብቻ ያልፈጸመላትን ማንኛዋንም ሴት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከእርስዋ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሊኖርህ የማትገባ ሴት”

ብልሹ ስነምግባር ያላት ሴት

ይህ አንድ ወንድ የማያውቃትን ማንኛዋም ሴት ያመለክታል፡፡

በለዘበ ቃሏ

ለማታለል የሚነገሩ ቃላት ለስላሳ እቃዎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን የምትናገር፣ ነገር ግን ልታታልልህ የምትፈልግ”