am_tn/pro/07/01.md

2.5 KiB

ቃሎቼን ጠብቅ

እዚህ መጠበቅ መታዘዝን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቃሎቼን ታዘዝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ትእዛዜንም በአንተ ውስጥ አስቀምጥ

እዚህ የእግዚአብሔር ትእዛዛት አንድ ሰው በመጋዘን ውስጥ እንደሚያሰስቀምጣቸው ዕቃዎች ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትእዛዛቴን በቃልህ አጥና/ሸምድድ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ትእዛዜን ጠብቅ

እዚህ መጠበቅ መታዘዝን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቃሎቼን ታዘዝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ዓይንህ ብሌን

የዓይን ብሌን ሰዎች ብዙ ጊዜ በፊታቸው የተለያየ ነገር ሲመጣባቸው በተለምዶ በደመነፍስ ጥበቃ የሚያደርጉለትና የሚከላከሉለት በዓይን ውስጥ ያለው ጥቁሩ የዓይን ክፍል ነው፡፡ እዚህ “የዓይን ብሌን” አንድ ሰው እጅግ ዋጋ የሚሰጠውና በሚገባ ጥበቃ የሚያደርግለት ማንኛውንም ነገር ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እጅግ ውድ እንደሆነው ንብረትህ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በጣቶችህ እሰራቸው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ፀሐፊው ወንድ ልጁ አንዳንድ የእግዚአብሔር ትእዛዛት በቀለበቱ ላይ ቀርፆ በጣቱ ላይ እንዲያደርገው ይፈልጋል ወይም 2) ፀሐፊው ወንድ ልጁ ቀለበቱን ሳይረሳ ሁልጊዜ እንደሚያደርገው እንደዚሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሁልጊዜ እንዲያስታውስ ይፈልጋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በልብህ ጽላት ጻፋቸው

እዚህ ልብ የሰውን አእምሮ ይወክላል፣ አንድን ነገር በሚገባ ማስታወስ ደግሞ ያ ሰው በድንጋይ ጽላት ላይ እንደጻፈው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህንን በምሳሌ 3፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በድንጋይ ላይ እንደጻፍካቸው እያሰብህ ትእዛዛቴን በሚገባ አስታውሳቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)