am_tn/pro/06/34.md

1.3 KiB

ቁጡ

በጣም መናደድ

እርሱ ምህረት አያደርግም

“እርሱ” የሚለው የሚያመለክተው ሚስቱ ከሌላ ወንድ ጋር ያመነዘረችው የአመንዝራይቱ ባል ወይም ጎረቤት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በአንተ ላይ የሚያመጣው ጉስቁልና ገደብ አይኖረውም” ወይም “የተቻለውን ያህል ይጎዳሃል” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

በሚበቀልበት ጊዜ

“በቀል በሚያደርስበት ጊዜ” ወይም “የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው በሚቀርብበት ጊዜ”

ይበቀላል

ሰውየው ሲበቀል፣ ቀድሞ የጎዳውን ሰው ለመጉዳት ነው

ካሳ

ይህ በደል ያደረሰው ሰው ለተበዳዩ የሚከፍለው ክፍያ ነው

እሺ አይልም

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእርሱን አእምሮ ለመለወጥ የሚችል በቂ ገንዘብ ልትከፍለው አትችልም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እሺ አይልም፣ ብታቀርብለትም

“እሺ አይልም፡፡ ብታቀርብለትም ይህ እውነት ነው”