am_tn/pro/06/24.md

2.3 KiB

እርሱ ይጠብቅሃል

እዚህ ላይ “እርሱ” የሚለው ቃል በምሳሌ 6፡20 ላይ በአባትና በእናት የተማራቸውን ትምህሮች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያድንሃል” ወይም “ይጠብቅሃል” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ምግባረ ብልሹ ሴት … አመንዝራ ሴት

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ “አመንዝራ ሴት” የሚለውን በምሳሌ 5፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

በሽፋሽፍትዎቿ እንድታጠምድህ አትፍቀድላት

ፀሐፊው የሴትን ሽፋሽፍቶች ወጣት ወንድ ልጅ ሊሳስት የሚችልበት ወጥመድ እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ እነዚህ ለውበቷ ተዛምዶአዊ ንግግር ዘይቤ ናቸው፣ በእርስዋ እንዲሳብና እርስዋን እንዲፈልጋት ለማድረግ ሴቷ ወጣት ወንድ ልጅን ለምታይበት መንገድ ደግሞ ምትክ ስም ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በቁንጅናዋና አንተን በዓይኖቿ በምታይበት ሁኔታ በቁጥጥር ስር እንድታደርግህ አትፍቀድላት” (ተለዋጭ፣ ተዛምዷዊ እና ምትክ ስም የሚለውን ተመልከት)

ምግባረ ብልሹ

“ክፉ ምግባር”

በልብህ

“ልቧ” አእምሮዋን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “በሃሳብህ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ውበቷ

“ስለ እርስዋ ያላት ውበት” ይህ ለሴቷ ምትክ ስም ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእርስዋ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

አያጥምድህ

“በቁጥጥር ስር አታድርግህ”

ሽፋሽፍትዎቿ

“ሽፋሽፍቶች” የወንድ ልጅ ቀልብ ለመሳብ የምትጠቀምበት በሰውነቷ ስለሚታዩ ማንኛውም ውበት የሚቆም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልከ መልካም ዓይኖቿ” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)