am_tn/pro/06/20.md

1.4 KiB

የአባትህን ትዕዛዝ ጠብቅ … የእናትህንም ትምህርት አትተው

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በአንድ በኩል ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ “አባት” እና “እናት” በሚሉት ድግግሞሽ አጽንዖት ሴቶችን በመማር ማስተማሩ ሂደት ውስጥ በግልጽ ያካትታል፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

የእናትህንም ትምህርት አትተው

ይህ የንግግር ዘይቤ አዎንታዊውን “ጠብቅ” ለማለት አሉታዊውን “አትተው” የሚለውን ተጠቅሟል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእናትህን ትምህርት ጠብቅ” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

ሁልጊዜ በልብህ አኑራቸው፣ በአንገትህም ዙርያ እሰራቸው

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እነዚህ ሐረጎች አንተን ለማስታወስ በሰውነትህ ውስጥ ወይም በሰውነትህ ላይ ልታስቀምጣቸው እንድትችል ትእዛዘቱና ትምህርቶቹ እንደተጻፉ አድርገው ይገልጿቸዋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በልብህ አኑራቸው

“ውደዳቸው” “ስለእነርሱ አስብ”