am_tn/pro/06/12.md

1.3 KiB

የማይረባ ሰው - ክፉ ሰው

እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው እናም ይህ ሰው ምን ያህል ክፉ እንደሆነ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምንም ዓይነት ጥቅም የሌለው ሰው - ክፉ ሰው” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

በጠማማ ንግግሩ ይኖራል

በዚህ ስፍራ ውሸት እንደ ጠማማ ንግግር ተገልጿል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ያለማቋረጥ ውሸት ይናራል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በዓይኑ ይጠቅሳል፣ በእግሩም ምልክት ያስቀምጣል እና በጣቶቹም ይጠቁማል

እነዚህ ሶስት ሐረጎች ክፉ ሰው ሌሎች ሰዎችን ለማታለል መልእክት በምስጢር የሚያስተላልፍበትን መንገድ ያብራራሉ፡፡

በዓይኑ ይጠቅሳል

አንድ ሰው በዓይኑ ከጠቀሰ፣ አንድ ዓይኑን በቅጽበት ጨፍኖ በመግለጥ ለሌላ ሰው ምስጢራዊ ምልከት ይሰጣል፡፡ ይህ እምነት የመጣል፣ የማረጋጋጫ ወይም የሌላ ነገር ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡