am_tn/pro/06/09.md

3.2 KiB

እስከ መቼ ትተኛለህ … ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?

አስተማሪው እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠቀመው ብዙ እንቅልፍ የሚተኛውን ሰነፍ ሰው ለመገሰጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ሰነፍ ሰው ንቃ! ከአልጋህ ውጣ!” (ትይዩነት እና መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ጥቂት ትተኛለህ … ጥቂት እጅህን ታጥፋለህ

እነዚህ ነገሮች ሰነፍ ሰው የሚናገራቸው ዓይነት ናቸው፡፡

ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂት ታንቀላፋለህ

እነዚህ ሃሳቦች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እንደ ሙሉ ዓረፍተ ነገር ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትንሽ ረዘም ላለ ጊዜ እተኛለሁ፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ ዘና ብየ ልተኛ፡፡” (ትይዩነት እና አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ለማረፍ እጅህን ታጥፋለህ

ሰዎች ብዙ ጊዜ የበለጠ ተመቻችተው ለማረፍ ጋደም ሲሉ እጆቻቸውን ያጥፋሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ተመቻችቼ እጆቼን አጥጥፋለሁ ከዚያም ለትንሽ ጊዜ አርፋለሁ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ድህነትህ ይመጣብሃል

ይህ የስንፍና ውጤት እንደሆነ ግልጽ ለማድረግ እንደ አዲስ አረፍተ ነገር መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰነፍ መሆንህን ከቀጠልህ ድህነትህ ይመጣብሃል” ወይም “በተኛህበት ድህነት ይመጣብሃል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ድህነትህ እንደ ወንበዴ ትመጣብሃለች

ሰነፍ ሰው በድንገት ድሃ የሚሆንበት መንገድ ልክ ወንበዴ በድንገት መጥቶ ሀብትን ሰርቆ የሚሄድበት ዓይነት መንገድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወንበዴ በድንገት መጥቶ ያለህን በሙሉ እንደሚሰርቅ እንደዚሁ በድንገት ድሃ ትሆናለህ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ወታደር

ሰነፍ ሰው በድንገተኛ መንገድ ችጋሩ የሚመጣበት አንድ የታጠቀ ወታደር ከአንድ ሰው ያለውን ሁሉ በድንገተኛ መንገድ እንደሚወስድበት ነው፡፡ ይህ እንደ ሙሉ ዓረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ችጋርህ እንደ ታጠቀ ወታደር ወደ አንተ ይመጣብሃል” ወይም “የታጠቀ ወታደር ወደ አንተ መጥቶ ያለህን ሁሉ እንደሚሰርቅብህ እንደዚሁ ችጋርህ ይመጣብሃል” (ተነፃፃሪ ዘይቤ እና አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

የታጠቀ ወታደር

“የጦር መሳርያ የያዘ ወታደር” ወይም “ የጦር መሳርያ የያዘ ሰው”