am_tn/pro/06/06.md

1.6 KiB

ተመልከት … አስተውል

“አጥና … አስብ” ወይም “በጥንቃቄ አስተውል … አሰላስል”

ጉንዳን

ጉንዳን ከምድር በታች ወይም ራሳቸው በሰሩት የአፈር ክምር የሚኖሩ ትንሽ ነፍሳት ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ በቡድን ተሰባስበው የሚኖሩና ከራሳቸው እጅግ የበለጡ ነገሮችን መሸከምና ማንሳት የሚሉ ናቸው፡፡

መንገዷን አስተውል

ይህ የጉንዳንን “መንገድ” በመጠቀም የጉንዳንን ባህርይ የሚያሳይ ዘይቤአዊ ንግግር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጉንዳን እንዴት እንደምትሰራ አስተውል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አለቃ፣ አዛዥ ወይም ገዢ

እነዚህ ሶስት ቃላቶች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ በአንድ ጉንዳን ላይ በመደበኛነት ስልጣን ያለው ማንም እንደሌለ አጽንዖት ለመስጠት ጥቅም ላይ የዋሉ ናቸው፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ምግቧን በበጋ ታዘጋጃለች … የምትበላውን በመከር ትሰበስባለች

እነዚህ ሁለት ቃላቶች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ የተደጋሙት ጉንዳን ምን ያህል ኃላፊነት የምትሸከም መሆኗን ለማሳየት ነው፡፡

በጋ

በጋ አንዳንድ ዛፎች ፍሬ የሚያፈሩበት የዓመቱ ወቅት ነው፡፡