am_tn/pro/06/04.md

1.8 KiB

ለአይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፡፡

“አይኖችህ አያንቀላፉ፤ ሽፋሽፍቶችህ አያንጎላጁ፡፡” እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው እናም የተደጋገሙት ሰነፍ መሆን እንደማይገባ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ የበለጠ አጽንዖት ለመስጠት በአሉታዊ መንገድ ተገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነቅተህ ጠብቅ፣ የምትችለውን ሁሉ አድርግ” (ትይዩነት እና ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

አይንህ … ሽፋሽፍቶችህ

ይህ የፊትን አካላት በመጠቀም የሰውን ሙሉ ሰውነት የሚያሳይ ዘይቤአዊ ንግግር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ራስህ … የአንተ ሰውነት” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

የሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ እንደምታመልጥ እንዲሁ ራስህን አድን፡፡

“ከአዳኝ እንደምታመልጥ የሜዳ ፍየል ከጎረቤትህ አምልጥ”

የሜዳ ፍየል

ይህ ሳር የሚበላና ብዙ ጊዜ ሰዎች ለምግብነት የሚያድኑት በጣም ትልቅና ቀጭን እንስሳ ነው፡፡ ይህ እንስሳ በፍጥነት በመሮጥ ችሎታው የታወቀ ነው፡፡

ከአዳኝ እጅ

የአዳኝ እጅ የአዳኙን በቁጥጥር ስር ማድረግ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከአዳኝ ቁጥጥር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ከአጥማጅ እጅ እንደምታመልጥ ወፍ

“ከወፍ ወጥመድ በርራ እንደምታመልጥ ወፍ አምልጥ”