am_tn/pro/06/01.md

1.3 KiB

ገንዘብህን ዋስ ሆነህ ብታስይዝ

እዚህ ላይ ቃል ኪዳንህና ሁኔታዎች ገንዘብህን እንድትቆጥብ አስገድደውሃል የሚል ሃሳብ አለው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተወሰነ ገንዘብህን እንድትቆጥብ አድርጎሃል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለጎረቤትህ ብድር ዋስ ብትሆን

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ጎረቤትህ ብድር ሊጠይቅህ ወደ አንተ መጥቶ ይሆናል” ወይም 2) ጎረቤትህ ከሌላ ሰው ብድር ለመውሰድ ፈልጎ ነገር ግን ጎረቤትህ ብድሩን መመለስ ባይችል በድሩን ለመክፈል ቃል ገብተህ ይሆናል”

ጎረቤት

ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለበት የዕብራይስጡ ቃል “ጓደኛ” የሚል ትርጉም አለው፡፡

በአፍህም ቃል ተጠምደህ ተይዘሃል

ይህ ዘይቤአዊ ንግግር አንተ ራስህን ልታስጠምድ ነው ይላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ራስህ የምጥጠመድበትን ወጥመድ ሰርተሃል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በአፍህ ቃል

“በተናገርከው” ወይም “ቃል በገባኸው”