am_tn/pro/05/20.md

2.4 KiB

ልጄ ሆይ፣ ስለምን በጋለሞታ ሴት ትማረካለህ፤ ስርአት የሌላትንስ ሴት ጡቶች ለምን ታቅፋለህ?

ፀሐፊው እነዚህን መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የጠየቀው ወንድ ልጁ እነዚህን ነገሮች ማድረግ እንደሌለበት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ልጁ ሆይ፣ በጋለሞታ ሴት አትማረክ! ስርአት የሌላትንስ ሴት ጡቶች አትቀፍ” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በጋለሞታ ሴት ትማረካለህ

ለሴት በሚኖር ፍላጎት የሚመጣ ጥልቅ መነሳሳት ልጁ በዚያች ሴት እንደመማረክ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጋለሞታ ሴት እንድትማርክህ ፍቀድ” ወይም “ጋለሞታ ሴት እንድታፈዝዝህ ፍቀድ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ስርአት የሌላትን ሴት ጡቶች ለምን ታቅፋለህ?

“እዚህ ላይ “ጡቶች” የሚለው ቃል ስርአት የሌላትን ሴትና ወሲባዊ ማራኪነትዋን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስርአት የሌላትን ሴት ለምን ታቅፋለህ”

ስርአት የሌላትን ሴት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ሚስትህ ያልሆነች ሴት” ወይም “የሌላ ሰው ሚስት የሆነች ሴት”

ሁሉንም ነገር ያያል … የሚሄድበትንም መንገድ ሁሉ ይመለከታል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ትርጉማቸው ተመሳሳይ ነው፣ እግዚአብሔር ማንኛውም ሰው የሚሰራውን ማኛውንም ነገር እንሚያውቅ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

የሚሄድበትንም መንገድ ሁሉ

ፀሐፊው የሰውን ድርጊት ወይም የሕይወት ዘይቤ አንድ ሰው የሚሄድበት መንገድ እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚሄድበት ቦታ ሁሉ” ወይም “የሚያደርገውን ነገር ሁሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)