am_tn/pro/05/18.md

2.8 KiB

ምንጭህ ቡሩክ ይሁን

ፀሐፊው የወንዱ ልጅ ሚስት ምንጭ እንደሆነች አድርጎ ተናግሯል፡፡ በዚህ ስፍራ “ብሩክ” የሚለው ቃል አንድ ሰው በሚስቱ ያለውን የደስታ ስሜት የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁልጊዜም ቢሆን ከሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጕብዝናህም ሚስት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ወጣት እያለህ ያገባሃት ሚስትህ” ወይም 2) “ወጣት ሚስትህ”

እንደ ተወደደች አጋዘን እንደ ተዋበችም ሚዳቋ

ፀሐፊው የወንድ ልጁን ሚስት “የተወደደች አጋዘን እና የተዋበች ሚዳቋ” እነደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ በዚህ ክፍል “አጋዘን” እና “ሚዳቋ” ትርጉሙ ሴት አጋዘን ነው፡፡ እነዚህ በመልካቸውም ሆነ በእንቅስቃሴአቸው የውበት ምልከት ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርስዋ እንደ አጋዘን እና እንደ ሚዳቋ ውብና ሞገስ የተሞላች ናት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞገስ የተሞላች

ይህ ቃል “ጸጋን የተሞላች” ማለት ኤደለም፣ “ስትንቀሳቀስ ውበት አላት” ለማለት ነው፡፡

ጡቶችዋ ሁልጊዜ ያርኩህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) የሚስት ጡቶች የባልን የወሲብ ፍላጎት ይቀሰቅሳል ይህም የሚስትን ሁለንተና አካልዋን የሚወክል ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጡቶችዋ ፍላጎትህን ያርኩ” ወይም “ ሰውነቷ ፍላጎትህን ያርካ” ወይም 2) ይህ ፀሐፊው የእናት ጡቶች የተራበ ልጅዋን እንደሚያረካ እንደዚሁ የሚስት ጡቶች የባልን ፍላጎት እንደሚያረኩ የተናገረበት ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ

ከሚስት ጋር የሚደረግ ወሲባዊ ፍቅር ጥልቅ ስሜትና ደስታባል ከፍቅር እንደጠጣ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህ በገቢር ግስ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አልኮል የሰከረን ሰው እንደሚቆጣጠር እንደዚሁ የሚስትህ ፍቅር ይቆጣጠርህ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በፍቅርዋ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “አንተ ለእርስዋ ባለህ ፍቅር” ወይም “እርስዋ ለአንተ ባላት ፍቅር”