am_tn/pro/05/15.md

2.8 KiB

ውኃ ከጕድጓድህ … የሚፈልቅ ውኃ ከምንጭህ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሰረታዊነት ትርጉማቸው አንድ ነው፡፡ ፀሐፊው ከሚስቱ ጋር ብቻ የሚተኛ ሰውን ከራሱ ጉድጓድና ምንጭ ብቻ ውኃ እንደሚጠጣ አድርጎ ተናግሯል፡፡ (ትይዩነት እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚፈልቅ ውኃ

ፀሐፊው አዲስ ወይም የሚፈልቅ ውኃን ውኃው እንደሚፈስ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አዲስ ውኃ” ወይም “የሚፈስ ውኃ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምንጮችህ … ወንዞችህ ወደ ሕዝብ አደባባይ ሊፈሱ ይገባልን?

ፀሐፊው እነዚህን መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የጠየቀው ልጁ እነዚህን ነገሮች ማድረግ እነደሌለበት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምንጮችህ … ወንዞችህ ወደ ሕዝብ አደባባይ ሊፈሱ አይገባም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ምንጮችህ … ወንዞችህ ወደ ሕዝብ አደባባይ ሊፈሱ ይገባልን?

እነዚህ “ምንጮችህ” እና “ወንዞችህ” የሚሉት ቃላት የወንድ የዘር ፈሳሽን የሚወክሉ ለስላሴ ዘይቤ ይመስላሉ፡፡ ለእነዚህ ተለዋጭ ሐረጎች ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት የሚከተሉት ናቸው፡- 1) ሰው ከሚስቱ ውጭ ከሌሎች ሴቶች ጋር መተኛት የአንድን ሰው ውኃ በሕዝብ አደባባዮች እንዲፈስስ መፍቀድ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ወይም 2) ሰው ከሚስቱ ውጭ ከሌሎች ሴቶች ልጆች መውለድ የአንድን ሰው ውኃ በሕዝብ አደባባዮች እንዲፈስስ መፍቀድ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ለስላሴ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሕዝብ አደባባዮች

እነዚህ በትልልቅ ወይም በትንንሽ ከተማዎች ሁለትና ከዚያም በላይ መንገዶች የሚገናኙበት ባዶ ቦታ ናቸው፡፡ ሰዎች እርስ በርሳቸው የሚገናኙበትና የሚነጋገሩበት የተለመዱ ቦታዎች ናቸው፡፡

እነርሱ ይሁኑ

“እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው “ምንጮችን” እና “ወንዞችን” እንደዚም ለቆሙለት ዓላማ ነው፡፡

ከአንተ ጋር ለሚገኙ እንግዶች አይሁኑ

“እነርሱን ከእንግዶች ጋር አትጋራ”