am_tn/pro/05/13.md

1.1 KiB

ጆሮየን ወደ አስተማሪዎቼ አዘነበልሁ

እዚህ “ጆሮ” የሚለው ቃል የሚያደምጠውን ሰው ይወክላል፡፡ ፀሀፊው አንድ ሰውን በትኩረት ማዳመጥን ጆሮ ለተናጋሪው ቅርብ እንዲሆን ወደሚናገረው ሰው አንገትን ማዝመም እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ በምሳሌ 4፡20 ላይ ይህን ተመሳሳይ ሐረግ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመለክት፡፡ (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በጉባኤው መካከል፣ በሕዝቡ ስብሰባ መካከል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ደግሞም 1) እግዚአብሔርን ለማምለክ ወይም 2) ለፈጸመው ክፉ ድርጊት ፍርድ ሊሰጡት በአንድ ላይ የተሰበሰቡትን የሰውየውን የማሕበረሰብ አካላት ያመለክታል፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)