am_tn/pro/05/09.md

2.5 KiB

በዚያ መንገድ

“እንዲህ ካደረግህ፡፡” ይህ ሀረግ በቀደመው ቁጥር ላይ የተናገረውን ያመለክታል፡፡

ክብርህን ለሌሎች አሳልፈህ አትሰጥም

“ክብር” ለሚለው ቃል ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉ፡- 1) ይህ የአንድን ሰው ዝና ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሌሎች ሰዎች መካከል ያለህን መልካም ዝና አታጣም” ወይም 2) ይህ የሰውን ሀብት እና ንብረት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሀብትህን ለሌሎች ሰዎች አሳልፈህ አትሰጥም” ወይም 3) ይህ ብርታትን ያመለክታል፣ የአንድን ሰው የሕይወት ግንባር ቀደም ዘመናት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የህይወትህን ምርጥ ጊዜያት ለሌሎች ሰዎች አሳልፈህ አትሰጥም”

ወይም የህይወት ዘመንህን ለጨካኝ ሰው

ፀሀፊው ያለጊዜው ምናልባትም በግድያ የሞተን ሰው የህይወቱን ዘመን ለሌላ ሰው አሳልፎ እንደሰጠው እቃ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ግሱ በፊተኛው ሀረግ የቀረበ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወይም የህይወት ዘመንህን ለጨካኝ ሰው ስጥ” ወይም “ወይም ጨካኝ ሰው እንዲገድልህ አድርግ” (አስጨምሬ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጨካኝ ሰው

ይህ ከአመንዝራዋ ሴት ጋር የተኛውን ሰው በጭካኔ የሚቋቋመውን የአመንዝራዋን ሴት ባል ሊያመለክት ይችላል፡፡

ባእድ ሰው በሀብትህ አይጠግቡም

ፀሀፊው የሌላ ሰውን ሀብት የወሰዱና የተጠቀሙበትን ሰዎች በሃብቱ እንደጨፈሩ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ባእድ ሰዎች ሀብትህን በሙሉ አይወስዱም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የደከምክበት ነገር ወደ ባእዳን ቤት አይሄድም

እዚህ ላይ “ቤት” የሚለው ቃል የዚያን ሰው ቤተሰብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያገኘሀቸው ነገሮች መጨረሻቸው የባእድ ቤተሰብ ንብረት አይሆኑም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)