am_tn/pro/05/07.md

2.1 KiB

አሁን

እዚህ ላይ አስተማሪው ስለ አመንዝራ ሴት ከማስጠንቀቅ ምክር ወደ መስጠት ተሸጋግሯል፡፡

አድምጠኝ….. ከማዳመጥ ፈቀቅ አትበል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተማሪው ትኩረት እንዲሰጥ ተመሳሳይ ሀሳብን ይገልፃሉ፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ከማዳመጥ ፈቀቅ አትበል

ፀሀፊው አንድ ድርጊት ማቆምን ያ ሰው በአካላዊ አቋም ከእርሱ ፈቀቅ ያለ እንደሆነ አስመስሎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማዳመጥ አታቁም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የአፌን ቃል

እዚህ ላይ “አፍ” የሚለው ቃል የሚናገረውን ሰው ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ቃሎች” ወይም “የምናገረውን” ( ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ምንገድህን ከእርስዋ አርቅ

እዚህ ላይ “መንገድ” የሚለው ቃል የሰውን የእለት ከእለት ተግባርንና ሁኔታን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራስህን ከእርስዋ አርቀህ ጠብቅ” ወይም” ከእርስዋ ራቅ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ቤትዋ በር አቅራቢያ አትምጣ

እዚህ ላይ “የቤትዋ በር” ቤቱን ራሱን ይወክላል፡፡ “አትምጣ” በሚለው ቃል ፈንታ “አትሂድ” የሚለውን ቃል መጠቀም በይበልጥ ተስማሚ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም የመጀመሪያው ተናጋሪው የእርስዋ በር ላይ እንደሆነ ሊያመለክት ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ቤትዋ በር አቅራቢያ አትሂድ” ወይም “ወደ ቤትዋ አቅራቢያ እንኳን ሳይቀር አትሂድ” (ተዛምዶአዊ እና የአትምጣ እና አትሂድ አጠቃቀም የሚለውን ይመልከቱ)