am_tn/pro/05/05.md

1.6 KiB

እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ

አዚህ ላይ “እግሮቿ” አመንዝራ ሴት ስትራመድ ይወክላል፡፡ ፀሀፊው ተግባሯን በመንገድ ላይ እየተራመደች እንዳለች አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ሞት የሚያመራ መንገድ ላይ እየተራመደች ነው” ወይም “የአኗኗር ዘይቤዋ ወደ ሞት ያመራል” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርምጃዎችዋ ወደ ሲኦል ይሄዳሉ

ፀሀፊው ተግባሯን በመንገድ ላይ እየተራመደች እንዳለች አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ሲኦል ትራመዳለች” ወይም “ተግባሯ ወደ ሲኦል ይወስዳታል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ ህይወት መንገድ አታስብም

ፀሀፊው ለሰው ረጅም ህይወት የሚሰጥ ባህርይ ወደ ህይወት የሚመራ መንገድ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ህይወት በሚመራው መንገድ ላይ መራመድን አታስብም” ወይም “ወደ ህይወት ስለሚመራ ተግባር አትጨነቅም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አረማመዷ የተቅበዘበዘ ነው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “አንደጠፋ ወዲህ እና ወዲያ ትቅበዘበዛለች” ወይም 2) “በተሳሳተ መንገድ ላይ ትጓዛለች”