am_tn/pro/05/03.md

2.6 KiB

የአመንዝራ ሴት ከንፈሮች ማርን ያንጠባጥባል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ከንፈሮች” የሚለው ቃል የአመንዝራ ሴት ቃሎችን ይወክላል እናም ፀሀፊው ቃላቶችዋ የሚስቡ መሆናቸው ከንፈሯ ማር የሚያንጠባጥቡ እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአመንዝራ ሴት ቃሎች ማር እንደሚያንጠባጥቡ ጣፋጭ ናቸው” ወይም 2) ፀሀፊው አመንዝራ ሴትን መሳም ስሜት መሳቡን የእርስዋ ከንፈሮች ማር እንደሚያንጠባጥቡ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አመንዝራ ሴት መሳም ከንፈሮቿ ማር እንደሚያንጠባጥቡ ጣፋጭ ነው” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አፏ ከዘይት ይበልጥ የለሰለሰ ነው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “አፍ” የሚለው ቃል የአመንዝራ ሴት ንግግርን ይወክላል ፀሀፊውም የንግግርዋን አሳማኝነት አፏ ከወይራ ዘይት የለሰለሰ አንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ንግግሯ አሳማኝ እና ከወይራ ዘይት የለሰለሰ ነው” ወይም 2) ፀሀፊው አመንዝራ ሴትን የመሳም ደስታ አፏ ከዘይት የለሰለሰ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእርስዋ መሳም ከወይራ ዘይት ይለሰልሳል” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በመጨረሻ ግን እንደ እሬት መራራ ናት

ፀሀፊው ከአመንዝራ ሴት ጋር ትስስር መጀመር የሚያመጣው ጉዳት እርስዋ እንደ እሬት የምትመር እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመጨረሻ ግን እርስዋ እንደሚመር እሬት ናት

እሬት

መራራ ጣእም ያለው ተክል

እንደ ስለታም ሰይፍ የሚቆርጥ

ፀሀፊው አመንዝራ ሴት ከእርስዋ ጋር ትስስር ያለው ሰው ላይ የምታስከትለውን ስቃይ እርስዋ ሰውየውን የሚቆርጥ ስለታም መሳሪያ እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለታም መሳሪያ እንደሆነች ሰውን ታቆስላለች” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)