am_tn/pro/05/01.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ፀሀፊው ልጆቹን እንደሚያስተምር አባት ይናገራል፡፡

ጆሮህን አዘንብል

እዚህ ላይ “ጆሮ” የሚለው ቃል የሚያዳምጠውን ሰው ይወክላል፡፡ ፀሀፊው አንድ ሰውን በትኩረት ማዳመጥን ጆሮ ለተናጋሪው ቅርብ እንዲሆን ወደሚናገረው ሰው አንገትን ማዝመም እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህንን በምሳሌ 4፡20 ላይ እንዴት እነደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በትኩረት አዳምጥ” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥንቃቄ

ጥንቃቄ ድርጊት እና ንግግርን በተመለከተ ጥንቁቅ የመሆን ችሎታ ነው፡፡ ይህንን በምሳሌ 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ከንፈሮችህ እውቀትን ይጠብቁ

እዚህ ላይ “ከንፈሮች” የሚለው ቃል የሚናገረውን ሰው ይወክላል፡፡ ፀሀፊው እውነተኛ የሆነውን ነገር ብቻ ለመናገር ጥንቁቅ የሆነ ሰውን የዚያ ሰው ከንፈሮች እውቀትን እየጠበቁ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እውነት የሆነውን ብቻ ትናገራለህ” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)