am_tn/pro/04/26.md

2.2 KiB

ለእግርህን ደልዳላ መንገድ አዘጋጅ

እዚህ ላይ “እግር” የሚለው ቃል የሚራመደውን ሰው ይወክላል፡፡ ፀሀፊው የሰውን ተግባር ያ ሰው በመንገድ እየተጓዘ እንደሆነ እና ያንን ተግባር በጥንቃቄ ማቀድን ደግሞ ያንን መንገድ ደልዳላ ማድረግ እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለመራመድ ደልዳላ መንገድን አዘጋጅ” ወይም “ማድረግ የምትፈልገውን ደህና አድርገህ አዘጋጅ” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ደልዳላ መንገድ

“ለስላሳ መንገድ” ወይም “የተስተካከለ መንገድ”

መንገድህ በሙሉ አስተማማኝ ይሆናል

ፀሀፊው የሰውን ተግባር ያ ሰው በመንገድ ላይ እየተጓዘ አንደሆነ እና እነዚያ ተግባሮች ስኬታማ መሆናቸውን መንገዱ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከዚያ የምታደርገው ሁሉ ትክክል ይሆናል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል

“ቀኝ” እና “ግራ” የሚሉት አቅጣጫዎች ወካይ ይመሰርታሉ፣ ትርጉሙም ሰው ደልዳላውን መንገድ በየትኛውም አቅጣጫ ሊተው አይገባውም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በቀጥታ ወደፊት ተራመድ ደልዳላውን መንገድንም አትተው” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

እግርህን ከክፉ መልስ

እዚህ ላይ “እግር” የሚለው ቃል የሚራመደውን ሰው ይወክላል፡፡ ፀሀፊው ክፉ ድርጊት አለማድረግን ሰው ከክፉ ርቆ እየሄደ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከክፉ ሽሽ” ወይም “ከክፉ ራቅ” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)