am_tn/pro/04/22.md

2.2 KiB

ቃሎቼ ህይወት ናቸው

ፀሀፊው የእርሱ ቃሎች የሰውን ህይወት መታደጋቸው እነዚያ ቃች የሰውየው ህይወት እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ቃሎች ህይወት ይሰጣሉ” ወይም “የተናገረኋቸው ነገሮች ህይወት ይሰጣሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ለሚያገኟቸው ለእነዚያ

ፀሀፊው ሙሉ በሙሉ የእርሱን ቃል መረዳት ሰው እነርሱን ፈልጎ እንደደሚያገኛቸው አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሚረዱአቸው እና ለሚተገብሯቸው ለእነርሱ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለመላው የእነርሱ ሰውነት ፈውስ ነው

“የእነርሱ” የሚለው ቃል “ለሚያገኟቸው ለእነዚያ” የሚለውን ይወክላል፡፡ የዚህ ሀረግ ባለቤት ከፊተኛው ሀረግ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቃሎቼ ለሚያገኟቸው ለሰውነታቸው በሙሉ ፈውስን ይሰጣሉ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ልብህን በጥንቃቄ ጠብቅ ከልለውም

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል የሰውን አእምሮ እና ሀሳብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አእምሮህን በጥንቃቄ ጠብቅ ሀሳብህንም ከልል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በመላው ትጋት

በማያቋርጥ እና በቅን ጥረት

የህይወት ምንጭ ከእርሱ ይፈልቃል

“እርሱ” የሚለው ቃል ለአእምሮ እና ለሀሳብ ምትክ ስም የሆነው ልብን ይወክላል፡፡ ፀሀፊው የሰውን ህይወት ከልብ የሚመነጭ ፈሳሽ ምንጭ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “የምትናገረው እና የምታደርገው ሁሉ ከሀሳብህ ይመጣል” ወይም “ሀሳቦችህ የህይወትህን መንገድ ይወስናሉ” (ምትክ ስም እና ተለዋጨ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)