am_tn/pro/04/20.md

1.4 KiB

ትኩረት ስጥ

“በጥንቃቄ አዳምጥ”

ወደ ንግግሮቼ ጆሮህን አዘንብል

እዚህ “ጆሮ” የሚለው ቃል የሚያደምጠውን ሰው ይወክላል፡፡ ፀሀፊው አንድ ሰውን በትኩረት ማዳመጥን ጆሮ ለተናጋሪው ቅርብ እንዲሆን ወደሚናገረው ሰው አንገትን ማዝመም እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ “ንግግሮች” የሚለው ቃል እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለምናጋራቸው ነገሮች ትኩረት በመስጠት አዳምጥ” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከአይኖችህ እንዲርቁ አታድርግ

ፀሀፊው ስለ አንድ ነገር ሁልጊዜ ማሰብን አንድ ሰው ሊያይ በሚችልበት ቦታ መጠበቅ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ “ስለ እነርሱ ማሰብ አታቁም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በልብህ ውስጥ ጠብቃቸው

ፀሀፊው አንድን ነገር ማስታወስ በልብ ውስጥ ማስቀመጥ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁልጊዜ አስታውሳቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)