am_tn/pro/04/18.md

2.7 KiB

የፃድቅ ሰዎች መንገድ…….. የክፉዎች መንገድ

ፀሀፊው የፃድቅ እና የክፉ ሰዎች ተግባር እና የአኗኗር ዘይቤ እነርሱ የሚራመዱበት “መንገድ” ወይም “አቅጣጫ” እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- የፃድቅ ሰዎች የአኗኗር ዘይቤ………. የክፉዎች የአኗኗር ዘይቤ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የፃድቅ ሰዎቸ መንገድ እየፈካ እንደሚሄድ የንጋት ብርሀን ነው

ፀሀፊው የፃድቅ ሰዎችን መንገድ ከፀሀይ መውጣት ጋር ያወዳድረዋል፤ ትርጉሙም እነርሱ የተጠበቁ ናቸው ምክንያቱም በሚራመዱበት ጊዜ የሚሄዱበትን ቦታ ለማየት የሚሆን ብርሀን አላቸው ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ፃድቅ ሰዎች በመንገዳቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ ይራመዳሉ ምክንያቱም የጠዋት ፀሀይ በመንገዳቸው ላይ ይበራል፣ እየፈካም ይሄዳል (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የንጋት ብርሀን

ይህ ንጋትን ወይም የፀሀይ መውጣትን ያመለክታል፡፡

ሙሉ ቀን እስኪመጣም ድረስ

ይህ ፀሀይ ይበልጥ ደማቅ ሆና የምትወጣበት የቀኑን ጊዜ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፀሀይ እጅግ ደምቃ እስክትወጣ ድረስ” ወይም “እስከ ሙሉ የቀን ብርሀን ድረስ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የክፉዎች መንገድ እንደ ጨለማ ነው

ፀሀፊው የክፉዎች መንገድን ከጨለማ ጋር ያወዳድራል፣ ትርጉሙም እነርሱ ሁልጊዜ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው ማለት ነው ምክንያቱም ወዴት እንደሚራመዱ ለማየት ብርሀን የላቸውም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ክፉ ሰዎች በመንገዳቸው ላይ በአደገኛ ሁኔታ ይራመዳሉ ምክንያቱም ለማየት የሚያስችል ብርሀን የላቸውም (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ በምን እንደሚሰናከሉ አያውቁም

ፀሀፊው መጎዳትን ሰው በሚጓዝበት መንገድ ላይ በሆነ ነገር መደናቀፍ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለምን እንደሚጎዱ እና መጥፎ አጋጣሚ እንደሚገጥማቸው አያውቁም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)