am_tn/pro/04/16.md

2.3 KiB

ክፋትን እስኪፈፅሙ ድረስ መተኛት አይችሉም

ምናልባት ቃል በቃል ሊተኙ ይችላሉ፣ ፀሀፊው ግን እንዴት ክፉ ተግባርን ለመፈጸም በብርቱ እንደሚፈልጉ ለመግለፅ ግነትን ተጠቅሟል፡፡ (ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እንቅልፋቸው አይመጣም

ፀሀፊው እንቅልፍ መተኛት ያልቻሉ ሰዎችን እንቅልፍ አንድ ሰው ከእነርሱ እንደሰረቀባቸው እቃ አድርጎ ይናገራል፡፡ አነርሱ ምናልባትም ቃል በቃል እንቅልፍ ሊተኙ ይችላሉ ነገር ግን ፀሀፊው ክፉ ተግባርን ለመፈጸም ምን ያህል አጥብቀው እንደሚሹ ለማስረዳት ግነትን ተጠቅሟል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መተኛት አይችሉም” (ግነት እና ጅምላ ፍረጃ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሰው እስኪያሰናክሉ ድረስ

ፀሀፊው ሌላ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስን ያን ሰው እንዲሰናከል ማድረግ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- አንድ ሰው እስኪጎዱ ድረስ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የክፋትን እንጀራ ይበላሉና የአመፃንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ይህ ፀሀፊው እነዚህ ሰዎች ሳያቋርጡ ክፋትን እና አመፃን የሚያደርጉ ሰዎች አንድሰው እንጀራ እና ወይንጠጅ እንደሚጠጣ እንደዚያ እንደበሏቸው እና እንደጠጧቸው አድርጎ የሚናገርበት ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ክፋት እንደሚመገቡት እንጀራ አመፅ ደግሞ እንደሚጠጡት ወይንጠጅ ነው፡፡ ወይም 2) እነዚህ ሰዎች ምግባቸውን እና መጠጣቸውን የሚያገኙት ክፋትን እና አመፃን በማድረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ክፉ ነገሮችን በማድረግ የሚያገኙትን እንጀራ ይበላሉ፣ በአመፅ ያገኙትንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)