1.3 KiB
1.3 KiB
ተግሳፅን ያዝ፣ አትተወውም
ፀሀፊው የተማረውን የሚያስታውስ ሰውን “ተግሳፅ” ያ ሰው አጥብቆ ሊይዘው የሚችለው ነገር እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያስተማርሁህን መታዘዝ ቀጥል እና መቼም ቢሆን አትርሳው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
እርሱ ህይወትህ ነውና
ፀሀፊው ምክር የሰውን ህይወት መጠበቁ የዚያ ሰው ህይወት እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ህይወትህን ይጠብቃልና” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
የክፉዎችን መንገድ አትከተል ደግሞም ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች መንገድም አትሂድ
ፀሀፊው የሰውን ተግባር ያ ሰው በመንገድ ላይ እየሄደ እንዳለ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች የሚያደርጉትን አታድርግ፣ ክፉ በሚያደርጉ ሰዎች ድርጊትም አትተባር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ሽሸው
“የክፉዎችን መንገድ ሽሽ”