am_tn/pro/04/10.md

1.5 KiB

ለቃሎቼ ትኩረት ስጥ

“የማስተምርህን በጥንቃቄ አዳምጥ”

በህይወትህ ዘመን ቡዙ አመታት ይኖሩሀል

“ቡዙ አመታትን ትኖራለህ”

በጥበብ ጎዳና አስተማርሁህ፤ በቀጥተኛ መንገዶች መራሁህ

ፀሀፊው ወንድ ልጁ በጥበብ እንዲኖር ማስተማሩ ወንድ ልጁን ሰው ጥበብ ሊያገኝ በሚችልበት መንገዶች እየመራው እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጥበብ መኖር እንዴት መኖ እንዳለብህ እያስተማርሁህ ነው፤ ለመኖር ትክክለኛውን መንገድ እያብራራሁ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በምትራመድ ጊዜ ማንም በመንገድህ ላይ አይቆምም፣ በሮጥህ ጊዜም አትሰናከልም

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ትርጉም ይጋራሉ፡፡ ፀሀፊው ሰው የሚያደርገውን ውሳኔ እና ተግባር ያ ሰው በመንገድ ላይ እየተራመደ ወይም እየሮጠ እንደሆነ እና ስኬታማ ስለሆነ ሰው ደግሞ መንገዱ ሰው እንዲሰናከል ከሚያደርግ መሰናክል ነፃ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ነገር ስታቅድ፣ እርሱን በማድረግ ስኬታማ ትሆናለህ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)