am_tn/pro/04/07.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

አባትየው የራሱ አባት ያስተማረውን ለልጆቹ ማስተማሩን አበቃ፡፡

ማስተዋልን ማግኘት እንድትችል ያለህን ሁሉ ክፈል

“ካለህ ነገር ሁሉ በላይ ለማስተዋል ዋጋ ስጥ”

ለጥበብ ከፍተኛ ስፍራ ስጥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሀለች

ፀሀፊው ጥበብ ሴት እንደሆነችና ለሰው ትልቅ ክብር መስጠቷን ያንንም ሰው ጥበብ ወደ ታላቅ ስፍራ እንዳወጣች አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለጥበብ ከፍተኛ ስፍራን ከሰጠህ ትልቅ ክብርን ትሰጥሀለች” (ሰውኛ ዘይቤ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከፍተኛ ስፍራን መስጠት

ለአንድ ነገር ወይም ለአንድ ሰው ታላቅ ፍቅር መሰማት ወይም ማሳየት

እርስዋን አጥብቀህ ስትይዛት ታከብርሀለች

ፀሀፊው ጥበብ ሴት እንደሆነች እና ለጥበብ ዋጋ የሚሰጥ ሰው ክንዱን በእርስዋ ዙሪያ እንዳሰቀመጠ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብን በጣም ከወደድህ ጥበብ ሰዎች እንዲያከብሩህ ታደርጋለች” (ሰውኛ ዘይቤ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በራስህ ላይ የክብር አክሊልን ታስቀምጣለች

ፀሀፊው ሰው ጥበብን ከማግኘቱ የተነሳ የሚኖረውን ክብር ጥበብ በግለሰቡ ራስ ላይ አክሊልን እንዳስቀመጠችለት አድረጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብ የአንተን ታላቅ ክብር የምታሳይ በራስህ ላይ እንደተቀመጠ አክሊል ትሆንልሃለች” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አክሊል

ከአበባ ወይም ከቅጠል ተሰካክቶ የተሰራ ክብ ቅርፅ ያለው ዘውድ

የተዋበ ዘውድን ትሰጥሀለች

ፀሀፊው ሰው ጥበብን ከማግኘቱ የተነሳ የሚኖረውን ክብር ጥበብ በግለሰቡ ራስ ላይ ዘውድን እንዳስቀመጠችለት አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ጥበብ በራስህ ላይ እንደሚሆን የተዋበ ዘውድ ይሆናል (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመላከቱ)