am_tn/pro/04/05.md

1.2 KiB

Possible

አባትየው የራሱ አባት ያስተማረውን ለልጆቹ ማስተማር ቀጥሏል፡፡

ጥበብ ማግኝት

“ጥበብን ለራስህ ለማግኘት ጠንክረህ ስራ” ወይም “ጥበብ አግኝ”

አትርሳ

“አስታውስ”

አትተው

“ተቀበል”

የአፌን ቃላቶች

እዚህ ላይ “አፍ” የሚለው ቃል የሚናገረውን ግለሰብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የምናገረውን” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብን አትተዋት እርስዋም ከለላ ትሆንሀለች፤ ውደዳት እርስዋም ትጠብቅሃለች

ፀሀፊው ጥበብ ታማኝ የሆነላትን ሰው የምትጠብቅ ሴት እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብን አትተዋት

ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብን አጥብቀህ ያዝ” ወይም “ለጥበብ ታማኝ ሁን”

ውደዳት

“ጥበብን ውደድ”