am_tn/pro/03/35.md

1.1 KiB

ጠቢብ ሰዎች ክብርን ይወርሳሉ

ፀሀፊው ጠቢብ ሰዎች የክብር ስም ማግኘታቸውን ክብርን በቋሚ ባለቤትነት እንደወረሱ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠቢብ ሰዎች ክብርን ያገኛሉ” ወይም “ጠቢብ ሰዎች የተከበረ ስም ያገኛሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሞኞች ከፍታ ውርደታቸው ይሆናል

ፀሀፊው እግዚአብሔር የሞኞች ውርደትን ለሁሉም ሰው ግልፅ ማድረጉን እግዚአብሔር ሞኞችን ሁሉም ሰው እንዲያያቸው ወደላይ ከፍ እንዳደረጋቸው አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ በገቢር/አድራጊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የሞኞትን ውርደት ሁሉም ሰው እንዲያይ ያደርጋል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)