1.2 KiB
1.2 KiB
የእግዚአብሔር እርግማን በክፉዎች ቤት ላይ ነው
ፀሀፊው የእግዚአብሔርን እርግማን በክፉ ሰው ቤት ጫፍ ላይ እግዚአብሔር እንዳስቀመጠው ነገር እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ “ቤት” የሚለው ቃል የቤተሰብ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የክፉ ሰውን ቤተሰብ ረግሟል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
የፃድቃን ሰዎችን ቤት ይባርካል
“ቤት” የሚለው ቃል ቤተሰብን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የፃድቅ ሰዎችን ቤተሰብ ይባርካል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ለትሁታን ሞገሱን ይሰጣል
ፀሀፊው የእግዚአብሔርን ሞገስ እርሱ ለሰዎች የሚሰጠው ነገር እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትረጉም፡- “ሞገሱን ለትሁት ሰዎት ያሳያል” ወይም “ለትሁት ሰዎች ጸጋውን ይሰጣል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)