1.3 KiB
1.3 KiB
በክፉዎች አማካኝነት የሚደርስ ጥፋት፣ ሲመጣ
ይህ በገቢር/አድራጊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉዎች ጥፋትን ሲያመጡ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ከጎንህ ይሆናል
“እግዚአብሔር ከአጠገብህ ይሆናል፡፡” አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጎን መቆም የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር አንዱ ሰው ሌላኛውን ሰው ይረዳዋል እና ይደግፈዋል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ይደግፍሀል እና ይከራከርልሀል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
እግርህ በወጥመድ እንዳይያዝ ይጠብቃል
ፀሀፊው “በሽብር” እና “በጥፋት” የተጎዳውን ሰው በወጥመድ እንደተያዘ አድርጎ ይናገራል፡፡ “እግር” የሚለው ቃል የሰውን ሁለንተና ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን ሊጎዱ ከሚፈልጉህ ሰዎች ይጠብቅሀል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)