am_tn/pro/03/23.md

1.7 KiB

በመንገድህ ላይ በደህንነት ትራመዳለህ

ፀሀፊው የአንድ ሰው ህይወትን መኖር ያ ሰው በመንገድ ላይ እየተራመደ እንዳለ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ህይወትህን በደህንነት ትኖራለህ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግርህ አይሰናከልም

“እግር” የሚለው ቃል የሰውን ሁለንተና ይወክላል፡፡ ፀሀፊው ስህተት ማድረግን ሰው በመንገድ ላይ በአንድ ነገር እንደተደናቀፈ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስህተት የሆኑ ነገሮችን አታደርግም” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በተጋደምህ ጊዜ

ሰው የሚጋደመው ለመተኛት እንደሆነ ያመለክታል፡፡ የዚህ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለመተኛት ስትጋደም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እንቅልፍህ ጣፋጭ ይሆናል

ፀሀፊው ስለ ሰላማዊ እና አስደሳች እንቅልፍ ለሚተኛው ሰው ጣፋጭ ጣእም እንደሚያስገኝለት አድርጎ ይናገራል፡፡ “እንቅልፍ” የሚለው ቃል እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንቅልፍህ አስደሳች ይሆናል” ወይም “በሰላም ትተኛለህ” (ተለዋጭ ዘይቤ ወይም ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)