am_tn/pro/03/21.md

1.4 KiB

እነርሱ ከእይታህ አይራቁ

ፀሀፊው አንድ ነገር አለመርሳትን ሁልጊዜ እርሱን ማየት እንደመቻል አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱን አትርሳ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለነፍስህ ህይወት ይሆናሉ

እዚህ ላይ “ነፍስ” ግለሰቡን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለአንተ ህይወት ይሆናሉ” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

በአንገትህ ዙሪያ የምታስረው የሞገስ ጌጥ

ፀሀፊው “ትክክለኛ ፍርድ” እና “ማስተዋል” አንድ ሰው በአንገቱ ዙሪያ እንደ አንገት ጌጥ የሚያስራቸው ነገሮች እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ ምስል እነዚህ አንድ ሰው ወደ ውጪ የሚያሳያቸው ዋጋ ያላቸው እንደሆኑ ይጠቁማል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ራሱን በአንገት ጌጥ እንደሚያስጌጥ እንደዚያ የሞገስ ማሳያ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሞገስ ጌጥ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “የሚስማማ ጌጥ” ወይም 2) “የእግዚአብሔርን ሞገስ የሚያሳይ ጌጥ፡፡”