am_tn/pro/03/17.md

1.2 KiB

መንገድዋ የደግነት መንገድ ነው፣ ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው

ፀሀፊው ጥበብ ሴት እንደሆነች እና ጥበብ ለሰው የምትሰጠው ጥቅም ያንን ሰው ጥበብ በመንገድ ላይ እየመራችው እንዳለች አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብ ሁልጊዜ በደግነት ትይዝሀለች እና ሰላም ትሰጥሀለች” (ሰውኛ ዘይቤ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርስዋ አጥብቀው ለሚይዟት የህይወት ዛፍ ናት

ፀሀፊው ጥበብን ህይወት የሚሰጥ ፍሬ እንደሚያፈራ ዛፍ እና ከጥበብ የሚጠቀም ሰውን ያም ሰው ከፍሬዋ እንደበላ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብ ከፍሬዋ የበሉትን ሰዎች በህይወት እንደምታቆይ ዛፍ ናት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የህይወት ዛፍ

“ህይወትን የሚሰጥ ዛፍ” ወይም “ፍሬው ህይወትን የሚያቆይ ዛፍ”

አጥብቀወ ለሚይዟት

“ፍሬውን አጥብቀው ለሚይዙ”