am_tn/pro/03/07.md

1.2 KiB

በራስህ አስተያየት ጥበበኛ አትሁን

ፀሀፊው የአንድ ሰውን አስተሳሰብ ያ ሰው በአይኑ አንድ ነገር እያየ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- በራስህ አስተሳሰብ ጥበበኛ አትሁን (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከክፉ ራቅ

ፀሃፊው ክፉ ተግባር አለመፈፀምን ከክፋት እየራቀ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፋትን አትፈፅም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ለስጋህ ፈውስ ይሆንልሀል

“እርሱ” የሚለው ቃል በቀደመው ቁጥር ላይ ፀሀፊው የሰጠውን ትእዛዛት ያመለክታል፡፡ የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልፅ መደረግ ይችላል፡፡ “ስጋ” የሚለው ቃል ሙሉ አካልን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህንን ካደረግህ ለአካልህ ፈውስ ይሆንልሀል” ( ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)