am_tn/pro/03/03.md

2.1 KiB

በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነት እና እውነተኛነት አይለዩህ

ፀሀፊው ስለ “የኪዳን ታማኝነት” እና “እውነተኛነት” አንድን ሰው ትተው መሄድ የሚችሉ ሰዎች እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ “ታማኝነት” እና “እውነተኛነት” የተባሉት ረቂቅ ስሞች “ታማኝ” እና “እውነተኛ” ተብለው ሊገለፁ ይችላሉ፡፡ እናም አሉታዊው ትእዛዝ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁልጊዜ እውነተኛ እና ለኪዳኑ ታማኝ ሁን” ( ሰውኛ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በአንገትህ ዙሪያ እሰራቸው

ፀሃፊው ስለ ታማኝነት እና እውነተኛነት አንድ ሰው እንደ አንገት ጌጥ በአንገቱ ዙሪያ የሚያስራቸው ነገሮች እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ አምሳያው እነዚህ አንድ ሰው ወደ ውጪ የሚያሳያቸው ዋጋቸው የከበረ ነገሮች እንደሆኑ ይጠቁማል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው የአንገት ጌጥ እንደሚያስረው እነርሱን በኩራት አሳያቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በልብህ ፅላት ላይ ፃፋቸው

እዚህ ላይ ልብ የአንድ ሰውን አእምሮ ይወክላል፡፡ አእምሮ አንድ ሰው መልእክት እና ትእዛዛትን መፃፍ የሚችልበት ፅላት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- በፅላት ላይ በቋሚነት እንደፃፍሃቸው እንደዚሁ ሁልጊዜ አስታውሳቸው (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔረ እና በሰው ፊት

እዚህ ላይ ፊት ፍርድን ወይም ምዘናን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- በእግዚአብሔር እና በሰው ዳኝነት (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)