am_tn/pro/03/01.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ፀሀፊው ግጥምን በመጠቀም ልጁን እንደሚያስተምር አባት ይናገራል፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ትእዛዛቴን አትርሳ

“ትእዛዛት” የሚለው ቃል እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያዘዝኩህን እንዳትረሳ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ትምህርቴንም በልብህ ጠብቅ

የፊተኛው ሀረግ በአሉታዊ አነጋገር ያለውን ይሄ ሀረግ በአዎንታዊ አነጋገር ይናገረዋል፡፡ እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል አእምሮን ይወክላል፡፡ “ትምህርቴን” የሚለው ቃል እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁልጊዜ ያስተማርኳችሁን አስታውሱ” (ትይዩነት እና ምትክ ስም እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ረጅም ቀኖችን እና የሕይወት ዘመናትን

እነዚህ ሁለት ሀረጎች አንድ አይነት ትርጉምን ይጋራሉ ደግሞ ረጅም ህይወት መኖርንም ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ረጅም እድሜ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)