am_tn/pro/02/20.md

2.1 KiB

ታዲያ

ፀሀፊው ማስተዋል እና ጥንቃቄን የማግኘት ውጤትን ይናገራል፡፡

በመንገድ ትሄዳለህ ……… ጎዳና ትከተላለህ

የአንድ ሰው ጠባይ በመንገድ ላይ እየተጓዘ እንዳለ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመንገዱ ትኖራለህ……..ምሳሌውን ተከተል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉዎች ከምድሪቱ ይቆረጣሉ

ፀሀፊው እግዚአብሔር ሰዎችን ከምድሪቱ ማስወገዱን አንድ ሰው ቅርንጫፍን ከዛፍ ላይ እንደሚቆርጥ እግዚአብሔር ሰዎቹን እየቆረጠ እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ ይህ በገቢር/አድራጊ መልኩ መገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ክፉዎችን ከምድሪቱ ያስወግዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉዎች ……… ታማኝነት የጎደላቸው

እነኚህ የስም ቅፅሎች እንደ ቅፅል ሊገለፁ የሚችሉ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- እነዚያ ክፉ የሆኑት…… እነዚያ ታማኝነት የጎደላቸው ወይም ክፉ ሰዎች…….. ታማኝነት የጎደላቸው ሰዎች (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ታማኝነት የሌላቸው ከእርስዋ ይቆረጣሉ

ፀሀፊው እግዚአብሔር ሰዎችን ከምድሪቱ ማስወገዱን አንድ ሰው ቅርንጫፍን ከዛፍ ላይ እንደሚቆርጥ እግዚአብሔር ሰዎቹን እየቆረጠ እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ ይህ በገቢር/አድራጊ መልኩ መገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ታማኝነት የሌላቸውን ከእርስዋ ያስወግዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)