am_tn/pro/02/18.md

1.5 KiB

ቤትዋ ወደ ሞት ይመራል

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “ወደ ቤትዋ መሄድ ወደ ሞት ይወስዳል” ወይም 2) “ወደ ቤትዋ የሚወስደው መንገድ ወደ ሞት የሚወስድ መንገድ ነው፡፡”

አካሄዷ ይመራሀል

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “ወደ ቤትዋ ያለው መንገድ ይመራሀል” ይህ ወደ ቤትዋ የሚያመራውን መንገድ ወይም ዱካ ይወክላል 2) ይህ ተለዋጭ ዘይቤ አኗኗርዋን እንደምትጓዝበት መንገድ አድርጎ የሚናገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአኗኗር መንገዷ ይመራሀል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በመቃብር ወዳሉት

ይህ የሙታንን መንፈስ ይወክላል ደግሞም ለሙታን መኖሪያም ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ መቃብር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ እርስዋ መግባት

ይህ አንድ ሰው ከሴተኛ አዳሪ ጋር እንደሚያደርገው ከእርስዋ ጋር ለመተኛት ወደ ቤትዋ መሄድ ማለት ነው፡፡ (ለስላሴ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የህይወትን መንገድ አያገኙም

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ወደ ህያዋን ምድር አይመለሱም” ወይም 2) “መቼም ቢሆን እንደገና ደስተኛ ህይወትን አይኖሩም፡፡”