1.3 KiB
1.3 KiB
ደስ ይሰኛሉ
እነርሱ የሚለው ምሳሌ 2፡12 ላይ ያሉትን ሰዎች ይወክላል
በክፉ ጠማማነት ሀሴት ማድረግ
ይህ ከመጀመሪያው የዐረፍተ ነገር ክፍል ጋር በመሰረቱ አንድ አይነት ትርጉም አለው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ እንደሆነ የሚያውቁትን በማድረግ ሀሴት ያደርጋሉ” (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)
ጠማማ መንገድን ይከተላሉ
ሌሎችን የሚዋሹ ሰዎች የተጣመመ ወይም የተጠመዘዘ መንገድ ላይ እንደሚጓዙ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሌላ ሰዎችን ያታልላሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
አካሄዳቸውን በአታላይነታቸው ይደብቃሉ
ሌሎች ሰዎች ምን እንዳደረጉ እንዳያውቁባቸው የሚዋሹ ሰዎች ማንም ሰው መንገድ ላይ እንዳያይከተላቸው አካሄዳቸውን እንደሸፈኑ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንም ሰው ያደረጉትን እንዳያውቅ ይዋሻሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)