am_tn/pro/02/11.md

2.1 KiB

ጥንቃቄ ይጠብቅሀል፣ ማስተዋልም ይጋርድሀል

“ጥንቃቄ” እና “ማስተዋል” አንድ ሌላ ሰውን መጠበቅ የሚችሉ ሰዎች እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ እነዚህ ሁለት ሀሳቦች በመሰረቱ አንድ አይነት ትርጉም አላቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ በጥንቃቄ ስለምታስብ እና ትክክል እና ስህተት የሆነውን ስለምትረዳ የተጠበቅህ ትሆናለህ” (ሰውኛ ዘይቤ እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ጥንቃቄ

በድርጊት እና ንግግር ጥንቁቅ የመሆን ችሎታ

ይጠብቅሀል

አንድን ሰው ወይም እንድን ነገር ለመጠበቅ፣ ለመከላከል ወይም ለመንከባከብ

እነርሱ ከክፋት መንገድ ያድኑሃል

“እነርሱ” የሚለው አንድን ሰው መጠበቅ የሚችሉ ሰዎች እንደሆኑ ተደርጎ የተነገረላቸው ጥንቃቄ እና ማስተዋልን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ከሆነው መራቅን ታውቃለህ” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከክፋት መንገድ

ክፉ ባህሪ ክፋት አንድ ሰው የሚራመድበት መንገድ ወይም አቅጣጫ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ትክክለኛውን መንገድ የተወ እና በጨለማ መንገድ የሚጓዝ

ትክክለኛ የሆነውን የማያደርግ ነገር ግን ክፉ የሆነውን ለማድረግ የወሰነ ግለሰብ በትክክለኛው መንገድ መጓዝ እንዳቆመ እና በጨለማው መንገድ መጓዝ እንደመረጠ ሰው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የተወ

“እርሱ” የሚለው ጠማማውን ነገር የሚናገሩትን ሰዎች ይወክላል፡፡

መተው

ወደ አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር ፈጽሞ ላይመለሱ ትቶ መሄድ