am_tn/pro/02/06.md

2.5 KiB

ከአንደበቱም እውቀት እና ማስተዋል ይወጣሉ

እዚህ ላይ “አንደበት” እግዚአብሔር ራሱን ወይም የሚናገረውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከእግዚአብሔር እውቀት እና ማስተዋል ይወጣሉ” ወይም “እግዚአብሔር ማወቅ እና ማስተዋል ያለብንን ይነግረናል” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ደስ ለሚያሰኙት ጥልቅ ጥበብን ያከማቻል

እግዚአብሔር ለሰዎች ጥበብ ማስተማሩ ጥበብ እግዚአብሔር የሚያከማቸው እና ለሰዎች የሚሰጠው ነገር እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሚያስደስቱት ለእነርሱ በእውነት ጠቢብ የሆነውን ያስተምራል፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም

“የሚያስተማምን”

ለእነርሱ ጋሻ ነው

እግዚአብሔር ህዝቡን መከላከል መቻሉ እርሱ ጋሻ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር እነርሱን ይከላከላል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያለነቀፋ ለሚሄዱ

ያለነቀፋ የሚሄድ ሰው ያለነቀፋ እንደሚራመድ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነቀፋ የሌለበት ሕይወት የሚኖር” ወይም “መኖር የሚገባቸውን ሕይወት የሚኖሩ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የፍትህን መንገድ ይጠብቃል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ፍትህ ራሱ መንገድ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ሰዎች በፍትህ መመላለሳቸውን ያረጋግጣል” ወይም 2) የሰው ህይወት መንገድ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በፍትህ የሚመላለሱትን እግዚአብሔር ይጠብቃል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእነርሱን መንገድ ያፀናል

የአንድ ሰው ህይወት መንገድ ወይም አቅጣጫ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚያን ይከላከላል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)