am_tn/pro/02/03.md

2.1 KiB

ማስተዋልን ለማግኘት ብትጣራ እና ድምፅህን ከፍ አድርገህ ብትጮህ

እነኚህ ሁለት ሀረጎች አንድ አይነት ትርጉም አላቸው፡፡ ግለሰቡ እግዚአብሔርን አጥብቆ ማስተዋልን እየለመነ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በአስቸኳይ እግዚአብሔርን ከጠየቅህ እና ማስተዋልን ከለመንክ” (ትይዩነት እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ድምፅህን ከፍ አድርገህ ብትጮህ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ጮክ ብሎ መናገር ወይም መጮህ ማለት ነው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እርስዋን ብር እንደምትፈልግ ብትሻት እና ማስተዋልን የተቀበረ ገንዘብን እንደምትፈልግ ብትፈልጋት

ሁለቱም ሀረጎች አንድ አይነት ትርጉም አላቸው፡፡ እነዚህ ተነፃፃሪ ዘይቤዎች አንድ ሰው ጠቢብ የሆነውን ለመረዳት ማድረግ የሚገባውን ፅኑ ጥረት ያሳስባሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዋጋ ያለው ነገርን ለማግኘት ጥረት በምታደርጉበት መጠን ማስተዋልን ብትፈልጉ” (ትይዩነት እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብትሻት……… ማስተዋልን ብትፈልጋት

ጥበብ የሆነውን ለመረዳት በጣም በፀና መሞከር አንድ ሰው መፈለግ ያለበት እቃ በሚገባ እንደመረዳት ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርን እውቀት ታገኛለህ

እግዚአብሔርን በማወቅ ስኬታማ መሆን የእግዚአብሔር እውቀት አንድ ሰው ከፍለጋ በኋላ የሚያገኘው ነገር እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)