am_tn/pro/02/01.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

አባት ልጁን ግጥም በመጠቀም ያስተምራል፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሎቼን ብትቀበል

“የማስተምርህን ብትሰማ”

ትዕዛዛቴን በአንተ ዘንድ ብታኖር

ለታዘዙት ነገር ዋጋ መስጠት ትዕዛዛቶቹ ሀብት እንደሆኑ እና ግለሰቡ ሀብቱን ለማስቀመጥ አስተማማኝ ቦታ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትዕዛዞቼ እንደ ሀብት ዋጋ እንዳላቸው አስብ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጆሮዎችህ እንዲያተኩሩ አድርግ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጥንቃቄ ለማዳመጥ ራስህን አስገድድ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብን

ይህ ረቂቅ ስም እንደ ቅፅል ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያስተማርኋችሁ ወዳለሁት ወደ ጥበብ ነገሮች” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ልብህን ወደ ማስተዋል አዘንብል

እዚህ ላይ “ልብ” የሰውን አእምሮ ይወክላል፡፡ “ልብህን አዘንብል” የሚለው ሀረግ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን አእምሮን ለአንድ ተግባር ሙሉ ለሙሉ መስጠት ወይም ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብ የሆነውን ለመረዳት ጠንክረህ ሞክር” ወይም “ጠቢብ አስተምሮዎችን ለመረዳት ራስህን ሙሉ በሙሉ ስጥ” (ምትክ ስም እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)