am_tn/pro/01/31.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ቀጥር 33 በምሳሌ 1፡22 ላይ የጀመረውን የጥበብ መግለጫ ይደመድማል፡፡

የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ

እዚህ ላይ የአንድ ግለሰብ ባህርይ መንገድ ወይም አቅጣጫ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም አንድ ሰው የባህሪውን ውጤት መቀበሉ ግለሰቡ የባህሪውን ፍሬ እየበላ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ድርጊታቸው የሚያመጣውን መዘዝ መለማመድ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእቅዳቸውም ፍሬ ይጠግባሉ

“የእቅዳቸውን ፍሬ እስከሚጠግቡ ድረስ ይመገባሉ፡፡” የተንኮለኛ ሴራውን ውጤት የሚቀበል ግለሰብ የእቅዱን ፍሬ እንደሚበላ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በተንኮለኛ ሴራቸው መዘዝ ይሰቃያሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አላዋቂ

ልምድ የሌለው ወይም የአእምሮ ብስለት የሌለው

መራቃቸው ይገድላቸዋል

ጥበብን የማይቀበል ግለሰብ በአካል ከጥበብ እንደ ራቀ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህ በገቢር/አድራጊ መልኩ ሊነገር ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለመማር ስላልፈቀዱ ሞቱ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰነፎችን ቸልተኛነታቸው ያጠፋቸዋል

“ቸልተኛ” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኞች ምን መደረግ እንደሚገባ ግድ ስለማይሰጣቸው ይሞታሉ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ቸልተኛነት

ስለ አንድ ነገር ፍላጎት ማጣት