am_tn/pro/01/26.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጥበብ በናቋት ላይ ምን እንደሚደርስ በማብራራት መናገሯን ቀጥላለች፡፡

እስቃለሁ

ጥበብ የምትባለው ሴት እርስዋን በማቃለላቸው ምክንያት በናቋት ላይ የምትስቅባቸው እንደሆነ ለማሳየት “ስለዚህ” የሚለውን ቃል በመጠቀም መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለዚህ እስቃለሁ” (አያያዥ ቃላት የሚለውን ይመልከቱ)

በመከራችሁ ላይ

“መጥፎ ነገር ሲደርስባችሁ”

ሽብር በመጣ ጊዜ

“ሽብር” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅፅል መገለፅ ይችላል፡፡ “በተሸበራችሁ ጊዜ” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

አስፈሪ ድንጋጤ እንደ ማዕበል በመጣባችሁ ጊዜ …… እንደ ዐውሎ ነፋስ ……. በመጣባችሁ ጊዜ

(ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) በሕዝቡ ላይ የደረሰው አስከፊ ነገር እነርሱን እንደመታቸው ማዕበል፣ ፍርሃትና መከራ ጋር ተነጻጽሯል፡፡

ዐውሎ ነፋስ

በጣም ሀይለኛ ጉዳትን የሚያስከትል የነፋስ ማዕበል