am_tn/pro/01/20.md

2.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

በ 1፡20-1፡33 ላይ ጥበብ ለህዝቡ እንደምትናገር ሴት ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብ ትጮሀለች

ቋንቋህ ጥበብን በከተማው ውስጥ ለህዝቡ እንደምትጮህ ሴት ለመጠቀም ካልፈቀደልህ እንደዚህ ብለህ መሞከር ትችላለህ፡- “እምዬ ጥበብ ትጮሀለች” ወይም “ክብርት ጥበብ ትጮሀለች” ወይም “ጥበብ እንደምትጮህ ሴት ናት” ( ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን የመልከቱ)

ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- በጉልህ ደምፅ ትናገራለች (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በአደባባይ

ይህ ቡዙ ሰዎች የሚገኙበት ቦታ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በገበያ ቦታዎች” ወይም “በከተማዋ ዋና አደባባዮች” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጩኸት በበዛባቸው ዋና ጎዳናዎች ላይ

እነዚህ አማጭ ትርጉሞች ናቸው፡- 1) “ዋና” የሚለው የተጨናነቁ ጎዳናዎች የሚገናኙበት ቦታ ያመለክታል ወይም 2) “ዋና” ጩኸት በበዛበት ጎዳና ላይ ያሉ ሰዎች ጥበብን ሊመለከቱ እና ሊሰሙ የሚችሉበት የግንብ ጫፍን ያመለክታል፡፡

እናንት አላዋቂዎች እስከመቼ አላዋቂነትን ትወዳላችሁ?

ጥበብ ይህንን ጥያቄ ጠቢብ ያልሆኑትን ለመገሰፅ ትጠቀምበታለች፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ አላዋቂዎች አላዋቂ መሆንን መውደድ ማቆም አለባችሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

አላዋቂ

ልምድ የሌለው ወይም የአእምሮ ብስለት የሌለው

እናንተ ፌዘኞች እስከመቼ በፌዝ ትደሰታላችሁ፣ እናንተ ሰነፎች እስከመቼ እውቀትን ትጠላላችሁ?

ጥበብ ፌዘኞችን እና ሰነፎችን ለመገሰፅ ይህንን ጥያቄ ትጠቀማለች፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ የምታፌዙ በፌዝ መደሰታችሁን ማቆም አለባችሁ፣ እና እናንተ ሰነፎች እውቀትን መጥላት ማቆም አለባችሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)