am_tn/pro/01/18.md

2.8 KiB

እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን ደም ለማፍሰስ ተደብቀው ይጠብቃሉ - በራሳቸው ላይ ወጥመድን ይዘረጋሉ

ይህ በምሳሌ 1፡17 የጀመረውን ንፅፅር ያጠናቅቀዋል፡፡ ኃጢአትን በመለማመድ ራሳቸውን እያጠፉ ያሉት ሰዎች ለራሳቸው ወጥመድ አጥምደው ራሳቸውን እንደ ገደሉ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነኚህ ሰዎች ግን ከወፎቹም የበለጠ ሞኝ ናቸው፡፡ ራሳቸውን በገዛ ወጥመዳቸው ገደሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን ደም ለማፍሰስ ተደብቀው ይጠብቃሉ

ተደብቆ መጠበቅ መሸሸግ ነው፣ ጭካኔን ለማድረግ መዘጋጀት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳቸውን ለመግደል ምቹ ጊዜ እንደ መጠባበቅ ነው” ወይም “ሌሎችን ለመግደል እየሞከሩ ስለሆነ እነርሱ ራሳቸው ይገደላሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የራሳቸውን ደም

እዚህ ላይ ደም ለአስከፊ ሞት ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ራሳቸውን በአስከፊ ሁኔታ ለመግደል (ምትክ ስም የሚለውን የመልከቱ)

በራሳቸው ህይወት ላይ ወጥመድን ይዘረጋሉ

እዚህ ላይ “የራሳቸው ህይወት” የሚለው ራሳቸው ለሚለው ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ራሳቸው የገዛ ራሳቸውን በድንገት አጥቅቶ ለመግደል በመጠባበቅ ላይ እንዳሉ የሚቆጠር ነው (ምትክ ስም የሚለውን የመልከቱ)

የሁሉም መንገዳቸው እንደዚህ ነው

የአንድ ሰው መድረሻ ወይም እጣ ፋንታ ልክ አንድ ሰው እንደሚራመድበት መንገድ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ ነው ሁሉም ሰው ላይ የሚደርሰው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ የተከማቸ ሀብት የባለቤቱን ህይወት ያጠፋል

ሀብትን በሀይል፣ በስርቆት እና በማታለል ለማግኘት በመሞከር ራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ሰዎች ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የተገኘው ሀብት ራሳቸውን እንደሚገላቸው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ የተገኘው ሀብት የባለቤቶቹን ህይወት እንደሚያጠፋ እንደዚያ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)