am_tn/pro/01/15.md

1.8 KiB

ከእነርሱ ጋር በዚያ መንገድ አትሂድ፤ እነርሱ በሚሄዱበት መንገድ እግርህ አይርገጥ

የሀጢያተኞችን ድርጊት እና ባህርይ አለመከተል ልጁ ሀጢያተኞች በሚሄዱበት መንገድ አለመሄዱ እና ፈፅሞም አለመንካቱ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሀጢያተኞች ጋር አትሂድ ወይም የሚያድርጉትን አታድርግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ

ሀጥያተኞች ክፉ ነገሮችን ለማድረግ ያላቸው ጉጉት ወደ ክፋት እየሮጡ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ነገሮችን ለማድረግ የተጠሙ ናቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግሮቻቸው ይሮጣሉ

እዚህ ላይ “እግር” የሚለው የሚወክለው ሙሉ ግለሰቡን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይሮጣሉ” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ደም ለማፍሰስ

እዚህ ላይ “ደም” የሚወክለው የሰውን ህይወት ነው፡፡ “ደም ለማፍሰስ” ማለት አንድ ሰውን መግደል ማለት ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን የመልከቱ)

ወፍ ፊት ለፊት እያየች እርስዋን ለመያዝ ወጥመድ መዘርጋት ጥቅም የለውም

ይሄ ተለዋጭ ዘይቤ ፊት ለፊት እያየች ያለውን ወጥመድ ያመለጠች ወፍን ጥበብ እና ለራሳቸው በሰሩት ወጥመድ ስር የወደቁ ሀጥያተኞችን ሞኝነት ያወዳድራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)