am_tn/pro/01/12.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ቁጥር 12-14 ሌሎች ሰዎች ሀጢያት እንዲሰሩ ለማባበል የሚሞክሩ የሀጢያተኞችን የሀሳብ ቃል ይጠቀልለዋል፡፡

ሲኦል ጤናማ ሰዎችን እንደሚውጣቸው እንዲሁ በህይወታቸው ሳሉ እንዋጣቸው

ሀጢያተኞች ልክ እንደ ሲኦል ንፁሀንን ስለ መግደል ያወራሉ፣ ህያው እና ጤነኛ ሰዎችን የሞቱ ሰዎች ወደሚሄዱበት ቦታ ይወስዳሉ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንዋጣቸው. . . . ሲኦል እንደሚውጥ

እዚህ ላይ መቃብር ሰዎችን እንደሚውጥና ወደ ሙታን ቦታ እንደሚወስድ ሰው ተመስሎ ይነገራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሲኦል ጤናማ ሰዎችን እንደሚውጣቸው

የሙታን መኖሪያ የሆነው ሲኦል ጤናማ ሰዎችን እንኳን እንደሚውጥ እንዲሁ ክፉዎች ሰለባዎቻቸውን ለማጥፋት ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ እናርጋቸው

ተቀባይነት ያላቸው ትርጉሞች እነዚህ ናቸው፡- 1) ማንም ሊያገኘው የማይችል፣ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የገቡ መንገደኞችን ያመለክታል ወይም 2) እዚህ ላይ “ጉድጓድ” የሚለው ቃል ሲኦል ወይም የሞቱ ሰዎች የሚገቡበት ቦታ ማለት ነው፡፡

ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ተቀላቀለን” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁላችንም አንድ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል

እዚህ ላይ “ቦርሳ” የሚወክለው የሰረቁትን ነገር በሙሉ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰረቅነውን በሙሉ እኩል እንካፈላለን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ቦርሳ

ገንዘብ ለመያዝ የሚሆን ከረጢት